top of page

ፌስቡክ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል የሚያስችል መገልገያ ይፋ አደረገ


የአለማችን ትልቁ ማህበራዊ ድረገፅ በፌስቡክ የሚተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል የሚያስችል መገልገያ ይፋ ተግባር ላይ ማዋሉን አስታወቀ፡፡

በፌስቡክ ላይ ይወጡ የነበሩ ሀሰተኛ መረጃዎች የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ማድረሱን በርካታ ተጠቃሚዎች ቅሬታ አቅርበው ነበር፡፡

ሀሰተኛ የሆኑ መረጃዎች ፌስቡክ ላይ ሲጫኑ ስለሀሰተኝነታቸው የሚገልፅ ምልክት አብሮ ለመውጣት የሚያስችል ስልት ተቀርፆለታል፡፡

ተቋሙ ያስተዋወቀው አዲሱ መለያም ቀድሞ "ስፓም" ወይንም "አኖይንግ" በሚል የሚታወቁትን መጠቆሚያዎች አይነት "it's a fake news story" የሚል አማራጭ አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም "disputed" የሚለውን አማራጭ አከራካሪ የሆኑና የ3ኛ ወገን ምልከታ የሚያስፈልጋቸውን መረጃዎች የሚያመለክት አማራጭም ተቀምጦለታል፡፡

ሀሰተኛ መረጃዎቹ ውሸት እንደሆኑ የሚያሳየው ምልክት አብሯቸው የሚወጣ ከሆነ ከመረጃው ጋር ተያይዞም ሀሰተኛ የተባለበትን ምክንያት የሚዘረዝር መረጃ ይያያዛል፡፡

አከራካሪ የሆኑና ሀሰተኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚጠረጠሩ መረጃዎችንም ሼር ከመደረጉ በፊት ስለሀሰተኝነታቸው የሚገልፅ ማስጠንቀቂያ ይኖረዋል፡፡

ፌስቡክ ሰዎች የራሳቸው ድምፅ እንዲኖራቸው እንደሚሰራና እውነተኛ መረጃዎችን በማጥራቱ ሂደትም ድምፅ እንዳይታፈን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚደረግ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ፈስቡክ ከዚህም ባሻገር የእውቅ የመረጃ ተቋማትን በማስመሰል ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ድረገፆችንም ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር መቀየሱንም አስታውቋል፡፡

የመረጃዎችን እውነተኛነት የሚያረግጡ 3ኛ ወገን ተቋማትም ምዝገባ እንደረደረገና እስካሁንም 43 ተቋማት ከተለያዩ አገራት መመዝገባቸውን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

የተመዘገቡት ተቋማት በምን መልኩ ወደ ስራ እንደሚገቡ ተጨማሪ ውሳኔ እንደሚያስፈልገውም ነው ድርጅቱ ያስታወቀው፡፡


Who's Behind The Blog
Recommanded Reading

Search By Tags

No tags yet.

Follow  ''ethiodailypost''

  • Facebook Social Icon
  • Twitter Social Icon
  • Google+ Social Icon
  • Instagram Social Icon
  • YouTube Social  Icon
  • RSS Social Icon
bottom of page