top of page

ኢትዮጵያዊው ምሁር የኢንጅነሪንግ ዘርፍ ተሻላሚ ሆኑ

November 16, 2016

ኤርባስ ግሩፕና ግሎባል ኢንጅነሪንግ ዲን ካውንስል በጋራ በመሆን የ2016 የኢንጅነሪንግ ምሁር ማዕረግን በአሜሪካ ሞርጋን ዩኒቨርስቲ መምህር ለሆኑት ኢትዮጵያዊ ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄ መስጠቱን ያሆ ኒውስ እና የዩንቨርስቲው ድረ-ገጽ ገልጿል፡፡

ምህሩ ሽልማቱን የወሰዱት ከ17 አገራት ለውድድር ከተመረጡ 40 ምሁራን ብልጫ ወስድው ነው፡፡

ሽልማቱ በደቡብ ኮሪያ ሴኦል ከተማ መስጠቱን ደረ-ገጹ አስፍሯል፡፡

ዶክተር ያዕቆብ በአፍሪካ የዘርፉን ትምህርት ለማሳደግ እያደረጉት ያለው አስትዋፅኦም አበረታች መሆኑን ዘገባው ያረዳል፡፡

በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ፣ በባህር ዳር፣ ጅማ እና በደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲዎች አገልግሎት እንደሚሰጡም የሞርጋን ዩንቨርስቲ ድረ-ገጽ ዘገባ ያስረዳል፡፣፡

ዶክትር ያዕቆብ አስታጥቄ በኢንጅንሪንግ ዘርፍ በሰጧቸው ግልጋሎቶች ሽልማት ሲያገኙ ይህ ለ6ኛ ጊዜ መሆኑ ሰፍሯል፡፡

እ.አ.አ በ2013 በአሜሪካ ከ27ሺህ በላይ የኢንጂነሪንግ ምሁራን ጋር ተወዳድርው የአሜሪካ ብሄራዊ ባለምጡቅ አምዕሮ የተባለውን ሽልማት ማግኘታቸውን ለትውስታ ዘገባው አስፍሯል፡፡

የሽልማቱ አላማ በመላው አለም ያሉ የኢንጅነሪንግ ባለሙያዎችን በማበረታታት ለፈጠራ እንዲነሳሱ ማድረግ እንደሆነ ተብራርቷል፡፡ ህዳር 8፣ 

Please reload

bottom of page